የብሪታንያ መንግሥትና ኢትዮጵያዊዉ የቀድሞ እስረኛ
ማክሰኞ፣ የካቲት 23 2002ማስታወቂያ
የብሪታንያ መንግሥት በአሸባሪነት ተጠርጥሮ ለዘጠኝ አመታት ያሕል በተለያዩ ሐገራት በታሠረዉ ኢትዮጵያዊ ወጣት ላይ ሥለተፈፀመዉ የግፍ ምርመራ የፅሁፍ መረጃ ለሕዝብና ለመገናኛ ዘዴዎች ይፋ አደረገ።ብሪታንያ በሚኖረዉ ቢንያም መሐመድ ላይ የተፈፀመዉን ግፍ የሚያትተዉ ሰነድ ይፋ እንዳይወጣ የብሪታንያ መንግሥት አጥብቆ ሲከራከር ነበር።የሐገሪቱ ይግባኝ ሰሚ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመንግሥትን የመከራከሪያ ነጥብና የበታች ፍርድ ቤቱን ዉሳኔን ዉድቅ አድርጎ ሰነዱ ይፋ እንዲሆን ከጥቂት ሳምንታት በፊ አዞ ነበር።የለንደኑ ወኪላችን ድል ነሳ ጌታነሕ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ድልነሳ ጌታነህ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ