1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቃዮች ቅሬታ

ሐሙስ፣ ግንቦት 9 2010

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው ባህር ዳር በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን የተጠለሉ ከ160 የሚበልሱ ሰዎች መንግሥት በክልላቸው ሊያቋቁማቸው ስላልቻለ ቅሬታ እያቀረቡ ነው። ባህር ዳር በገቡበት የመጀመሪያዎቹ ቀናት ከመንግሥት የምግብ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2xtOh
Äthiopien Amharas aus Benishangul vertrieben
ምስል DW/Yohannes Gebreegziabher

ይሁንና፣ ተፈናቃዮቹ ወደመጣችሁበት ተመለሱ በሚል ያካባቢው መንግሥት የያዘው አቋም እንዳስቆጣቸው  ገልጸዋል። የክልሉ አደጋ መከላከል እና የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በበኩሉ መጠለያ እና ምግብ አዘጋጅቶ ተፈናቃዮቹን ለመርዳት ያደረገው ጥረቱ በተፈናቃዮች ዘንድ ተቀባይነት እንዳላገኘ ገልጿል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር 

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ