የቤንሻንጉል ተመላሾች ስጋት
ማክሰኞ፣ ግንቦት 20 2011ማስታወቂያ
ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በምስራቅ ወለጋ ለወራት ተጠልለው የቆዩ ነዋሪዎች ወደ ቀድሞ አካባቢያቸው ቢመለሱም አሁንም የጸጥታ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ለዶይቼ ቬለ ገልጹ። ከተመላሾቹ መካከል የተወሰኑቱ ተመልሰው ወደ ሌላ መጠለያ ለመግባት መገደዳቸውን ተናግረዋል። በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ተጠልለው የነበሩ የተለያዩ የማህብረሰብ ክፍሎች ወደ ቀያቸው የተመለሱ ቢሆንም አሁንም የጸጥታ ስጋት እንዳለባቸው እና አንዳንዶች ደግሞ ቤታቸው በመቃጠሉ በመጠለያ ውስጥ ለመኖር ተገድደናል ይላሉ። ዝርዝሩን የአሶሳው ወኪላች ነጋሳ ደሳለኝ አሰናድቷል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ተስፋለም ወልደየስ
ሸዋዬ ለገሠ