የቤኒ ሻንጉል መስተዳድር ተቃዋሚዎችን ሾመ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 16 2014ማስታወቂያ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲ፣ የቤኒሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቃ (ቤሕነን) የክልሉ መንግስት በቅርቡ ለፓርቲዉ ባለስልጣናት የሰጠዉን ሹመት እንደማይቀበል አስታወቀ።የቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ባለፈዉ ሳምንት የስድስት ተቃዋሚ ፓርቲ ባለስልጣናት ሾሞ ነበር።አባሎቻቸዉ ከተሾሙላቸዉ ፓርቲዎች የተወሰኑት ሹመቱን ተቀብለዉታል።የቤኒሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ሶስት ባለስልጣናቱ ተሾመዉ ነበር።ይሁንና ፓርቲዉ ሹሙቱን «ያልተመከረበት»ና «የማናዉቀዉ» በማለት ዉድቅ አድርጎታል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ