የቤችን ማጂ ዞን ተፈናቃዮች
ረቡዕ፣ ሐምሌ 29 2001ማስታወቂያ
ሰዎቹ አዲስ አበባ በሚገኘዉ አዲስ ከተማ ትምህርት ቤት መጠለላቸዉ ነዉ የተነገረዉ። ይህን ዘገባ ለማጠናቀር መነሻ የሆነን ባለፈዉ ሰሞን ከአንድ አድማጫችን የደረሰን የስልክ መልዕክት ነዉ፤ ለጥቆማዉ የተከበሩ አድማጫችንን ከልብ እናመሰግናለን። ጉዩን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ለማጣራት ሞክሯል፤ ተፈናቃዮቹንና የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልላዊ መንግስት የህዝብ ግንኑነት ኃላፊ የሆኑትን አቶ አለሙ ዘዉዴን አነጋግሯል።
ታደሰ እንግዳዉ/ሸዋዬ ለገሠ/ተክሌ የኋላ