1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባላደራ ምክር ቤት ዕቅድ

ዓርብ፣ ጥር 1 2012

አቶ እስክንድር ነጋ ዛሬ እንዳስታወቁት አምና መጋቢት የተመሠረተዉ ምክር ቤት የፊታችን ሰኞ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲነት እዉቅ እንዲሰጠዉ ይጠይቃል።

https://p.dw.com/p/3W06q
Äthiopien Eskinder Nega
ምስል DW/S. Muchie

የባለአደራ ምክር ቤት የምርጫ ዕቅድ

የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት  ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት በይፋ መለወጡን የምክር ቤቱ ሰብሳቢ እስክንድር ነጋ አስታወቁ።አቶ እስክንድር ነጋ ዛሬ እንዳስታወቁት አምና መጋቢት የተመሠረተዉ ምክር ቤት የፊታችን ሰኞ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲነት እዉቅ እንዲሰጠዉ ይጠይቃል። አቶ እስክንድር ለጋዜጠኞች እንደነገሩት ፓርቲያቸዉ በሚቀጥለዉ ምርጫ አዲስ አበባ ዉስጥ የሚወዳደሩ ዕጩዎችን ያቀርባል፤ ከሌሎች ሐገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር «ሐገራዊ አማራጭ» የሚሆን ጥምረት ወይም ቅንጅት ይመሰርታልም። 

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ