የባህር ላይ ውንብድናን አስመልክቶ በዱባይ የተከፈተው ጉባኤ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 11 2003ማስታወቂያ
ሰኞ ዕለት የተከፈተው ይሄው ጉባኤ፤ የባህር ላይ ውንብድና የደቀነውን ችግር በዓለም አቀፉ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ፤ ማጉላት እንዳለበት፤ በሐምቡርግ ከተማ የሚገኘው «የጀርመን የንግድ መርከቦች ማህበር» ቃል አቀባይ ማክስ ጆንስ ለጆቼ ቬለ አስረድተዋል። በዱባይ ጉባኤ ላይ የተገኙት የሱማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር፤ ሞሀመድ አብዱላሂ ኦማር፤ የባህር ላይ ውንብድናን ለመታገል ይቻል ዘንድ፤ በሱማሊያ ሁኔታዎች መረጋጋይ ይኖርባቸዋል፤ ለዚህም የውጭ ሀገራት እርዳታ አስፈላጊ እንደሚሆን ገልፀዋል። «የጀርመን የንግድ መርከቦች ማህበር» ቃል አቀባይ ማክስ ጆንስ ከጉባኤው የሚጠብቁትን ከዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
ነጋሽ መሐመድ