«የባህል አምባሳደር» ስለሺ ደምሴ
እሑድ፣ ሰኔ 26 2008ማስታወቂያ
ከአንድ ወር ግድም በፊት ነዉ አርቲስት ስለሺ ደምሴ በጀርመናዉያን ተጋብዞ ኢትዮጵያዉያን ባቀረቡት የስዕል አዉደ-ርዕይ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ ሙዚቃዉን እንዲያቀርብ ተጋብዞ ነዉ እዚሁ ጀርመን ዉስጥ በአጋጣሚ ያገኘነዉ። በዩኤስ አሜሪካ ወደ 30 ዓመት ከኖረ በኋላ ኢትዮጵያ ጠቅልሎ የገባዉ አርቲስት ስለሺ ደምሴ ጀርመንም ቢሆን በየጊዜዉ ሲመላለስ 25 ዓመት እንዳስቆጠረ ነግሮናል። ሙዚቃዎቹ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ባህልን በማሳየቱ ሙዚቃህ ስዕል ነዉ ለሚሉኝ፤ አዎ ስዕል ነዉ ስል እገልፃለሁ ሲል አርቲስት ስለሺ ተናግሮአል። አገር ቤት መድረክ ላይ ከክራሩ ጋር ከሚቀርብበት ይልቅ በተለያዩ የዓለም ሃገራት እየተጋበዘ የሚሄድበት ጊዜ ይበልጣል። በዊጭ ሃገር መድረክም ላይ እየተዘዋወረ ሲያዜም ያምራል ሀገሬ ይላቸዋ፤ ለጋባዦቹ፤ በእንጊሊዘኛም ይተረጉምላቸዋል፤ በፈረንሳይኛም ካስፈልገ ካልሆነ ደግሞ አብረዉ እንዲዘፍኑም ያደርጋል። ታድያ እንዲህ እያለ መድረኩን ታዳሚዉን በመቶ በመቶ ተቆጣጥሮ በኢትዮጵያዉያን ባህላዊ ሙዚቃ ታዳሚዉን ያስደስታል። ምን አይነት ችሎታ ነዉ? ዘዴዉ ምን ይሆን? ስንል ሙዚቀኛ ስለሺ ደምሴን ጠይቀናል። ሙሉዉን ቅንብር ፤ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመቻን ይከታተሉ።
አዜብ ታደሰ