1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡድን ስምንት ጉባኤ መክፈቻ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 1 2001

የመጀመሪያው ቀን ጉባኤያቸው በተለይ በዓለም የምጣኔ ሀብት ቀውስና በአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም በኃይል ምንጭ ጉዳዮች ላይ አትኩረው ተወያይተዋል

https://p.dw.com/p/IjpE
ምስል AP

ቡድን ስምንት በመባል የሚጠሩት የዓለም ባለፀጋዎቹ መንግስታት መሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ ዛሬ ላክዊላ ኢጣላያ ውስጥ በከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ ተጀምሯል ። መሪዎቹ በዛሬው የመጀመሪያው ቀን ጉባኤያቸው በተለይ በዓለም የምጣኔ ሀብት ቀውስና በአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም በኃይል ምንጭ ጉዳዮች ላይ አትኩረው ተወያይተዋል ። በዚህ ጉባኤ ላይ ዘጠነኛ መሪ ሆነው ለመካፈል የተጋበዙትና ትናንት ኢጣልያ የገቡት የቻይናው ፕሬዝዳንት ሁ ጂንታኦ ግን ሀገራቸው ውስጥ በተፈጥረው ግጭት ምክንያት ጉባኤውን ላይ ሳይገኙ ዛሬ ጠዋት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ። ተክለ እግዚ ገብረ እግዚአብሄር ከሮም በቡድን ስምንት ጉባኤ አጀንዳና ከጉባኤ በሚጠበቀው ውጤት ላይ ያተኮረ ዘገባ አለው ።

ተክለ እግዚ ገ/እየሱስ

ነጋሽ መሐመድ