1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡድን ሀያ ጉባኤ ፍፃሜ

ዓርብ፣ መጋቢት 25 2001

ትናንት ለንደን ብሪታኒያ የተካሄደው የቡድን ሀያ ጉባኤ ፣ ዓለም ዓቀፉን የኤኮኖሚ ቀውስ ለመታደግ ለዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ድርጅት IMF እና ለሌሎች የገንዘብ እና የንግድ ተቋማት ከፍተኛ የገንዘብ ወጪ ለማድረግ በመስማማት ተጠናቋል ።

https://p.dw.com/p/HPpN
ምስል AP

በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ እንደተመለከተው በኢኮኖሚው ቀስው ሰበብ በመንገዳገድ ላይ ያሉ አገራትን ለሚረዱት ለIMF ና ለሌሎች የገንዘብ ተቋማት ከአንድ ትሪሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ዕርድታ ለመስጠት ቡድኑ ተስማምቷል ። ጉባኤው ከዚህ ሌላ ቀረጥ ያልተከፈለበትን ገንዘብ የሚያስቀምጡ ባለሀብቶች ባንኮችና ሀገራት ላይ የተጠናከረ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ አስታውቋል ። የጉባኤው ውጤት ከተሳታፊዎቹ አብዛኛዎቹን አርክቷል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኃላ