1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበጀት ቀመር ድልድል አዋጅ

ረቡዕ፣ የካቲት 27 2011

ላለፉት 3 ዓመታት ሲያገለግል የነበረው የበጀት ቀመር ድልድል እስከ 2012 ብቻ የሚያገለግል ሲሆን የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት የሃብት ክፍፍልን የተመለከተው ጉዳይ ፍተሻ እየረደረገበት በመሆኑ  አሰራሩን የሚመለከት በአዋጅ ደረጃ የሚወጣ ህግ ለማዘጋጀት ምክክር እየተደረገ ነው ።

https://p.dw.com/p/3EYs0
Äthiopien - Addis Abeba - City Churchill Road
ምስል DW/Y. Geberegziabehr

የኢትዮጵያ የፌደሬሽን ምክር ቤት እስካሁን የበጀት ክፍፍል የሚያደርግ ቀመር ለ 7 ጊዜ ያዘጋጀና እያሻሻለ ጥቅም ላይ ያዋለ ቢሆንም ወጥ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ እንዳልነበረው ነው የሚነገረው ፡፡  ይህም በመሆኑ ከተለያዩ አካላት የበጀት ፍትሃዊነት ጥያቄዎች እንዲነሱና ክልሎች ተደጋጋሚ የበጀት ድጎማ እና የገንዘብ ጥያቄዎችን እንዲያነሱ ሲያደርጋቸው ቆይቷል ። ላለፉት 3 አመታት ሲያገለግል የነበረው የበጀት ቀመር ድልድል እስከ 2012 ብቻ የሚያገለግል ሲሆን የፌዴራል እና የክልል መንግስታት የሃብት ክፍፍልን የተመለከተው ጉዳይ ፍተሻ እየረደረገበት በመሆኑ  አሰራሩን የሚመለከት በአዋጅ ደረጃ የሚወጣ ህግ ለማዘጋጀት ምክክር እየተደረገ ነው ።ሕጉ ውይይት ከተደረገበት በሁዋላ በአሰራሩ ላይ የሚታዩ ችግሮችን በሚያስወግድ መንገድ ተዘጋጅቶ ይቀርባል ተብሏል፡፡ የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ሰሎሞም ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ