የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሠራተኞች ክስ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 29 2011ማስታወቂያ
26 የቀድሞ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተከሰሱ። አቶ ጌታቸው አሰፋ ጉዳያቸው ነገ ይታያል ተብሏል። 46 ክሶች ከተመሰረተባቸው የቀድሞ የደኅንነት ባለሥልጣናት እና ሠራተኞች መካከል 22ቱ በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ ናቸው። ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ ሚያዚያ 29 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. በከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ክስ እንደተመሰረተባቸው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል።
ዮሐን ገብረእግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ