1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ወታደራዊ የደሕንነት ኮሎኔል ሰቆቃ

ረቡዕ፣ የካቲት 6 2011

መኮንኑ በ2008 ማብቂያ ከታሰሩ በኋላ ከፍተኛ ስቃይ ሲፈፀምባቸዉ እንደነበር አስታዉቀዋል።በዚሕ ዘገባ ስማቸዉን ያልጠቀስናቸዉ የቀድሞ መንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በየእስር ቤቱ እየዞሩ እስረኞችን ሲያስገድሉ፣ሲያስደበድቡ፤ አካሎቻቸዉን ሲያስቆርጡ ማየታቸዉንም  አስታዉቀዋ

https://p.dw.com/p/3DJWI
Burundi, Symbolbild Folter
ምስል picture-alliance/AP Photo/J. Delay

(Q&A) The Agony of the former Ethiopian Militery security Colonel - MP3-Stereo

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መንግስት የደሕንነት ባልደረቦች ሥርዓቱን የሸሹ ስደተኞችን አሁንም አዉሮጳ ድረስ እየተከታተሉ እንደሚያጠቁ አንድ የቀድሞ ወታደራዊ ደሕንነት ከፍተኛ መኮንን አስታወቁ።«ቴዎድርስ» በሚል ተለዋጭ ስም የሚጠሩት ሌትናንት ኮሎኔል እንደሚሉት አዉሮጳ የሚገኙት የቀድሞ መንግስት ሰላዮች አሁንም እሳቸዉንና ሌሎች ስደተኞን ማስፈራራታቸዉን አላቆሙም።መኮንኑ በ2008 ማብቂያ ከታሰሩ በኋላ ከፍተኛ ስቃይ ሲፈፀምባቸዉ እንደነበር አስታዉቀዋል።በዚሕ ዘገባ ስማቸዉን ያልጠቀስናቸዉ የቀድሞ መንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በየእስር ቤቱ እየዞሩ እስረኞችን ሲያስገድሉ፣ሲያስደበድቡ፤ አካሎቻቸዉን ሲያስቆርጡ ማየታቸዉንም  አስታዉቀዋል።ሌትናንት ኮሎኔል ቴዎድሮስን ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል ገሚሱን እናሰማችሁ።

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለስ