1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞዉ የቱኒዝያ ፕሬዚዳንት ቤን አሊ ታመዋል

ዓርብ፣ መስከረም 2 2012

ከስልጣን የተወገዱትና በስደት ሳዉዲ አረብያ የሚገኙት የቀድሞ የቱኒዝያ መሪ ዜን አብዲን ቤን አሊ ታመዉ ሆስፒታል መግባታቸዉ ተሰማ። በጎርጎረሳዉያኑ 2011 ዓም አምባገነን ተብለዉ በሕዝብ ስልጣን የተባረሩት የቱኒዝያ ፕሬዚዳንት ጠበቃ እንደገለፁት « የዜን አብዲን ቤን አሊ ጤንነት ሁኔታ ከባድ፤ ግን ለሕይወት የሚያሰጋ  አይደለም ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3PZhf
Tunesien ehemaliger Präsident Zine el-Abidine Ben Ali
ምስል picture-alliance/dpa

ከስልጣን የተወገዱትና በስደት ሳዉዲ አረብያ የሚገኙት የቀድሞ የቱኒዝያ መሪ ዜን አብዲን ቤን አሊ ታመዉ ሆስፒታል መግባታቸዉ ተሰማ። በጎርጎረሳዉያኑ 2011 ዓም አምባገነን ተብለዉ በሕዝብ ስልጣን የተባረሩት ቀድሞዉ የ83 ዓመቱ የቱኒዝያ ፕሬዚዳንት ጠበቃ እንደገለፁት « የዜን አብዲን ቤን አሊ ጤንነት ሁኔታ ከባድ፤ ግን ለሕይወት የሚያሰጋ  አይደለም ብለዋል። በሕዝብ ግፊት ከስልጣን ተወግደዉ ከቱኒዝያ ወደ ሳዉዲ አረብያ የተሰዱት ቤን አሊ፤ በሳዉዲ አረብያ ለሕዝብ እንብዛም ታይተዉ እንደማያዉቁና፤ እንደ ሌሎች የእድሜ ባለጠጎች ሁሉ ሕመምተኛ እንደሆኑ ተዘግቦአል። የቀድሞዉን ፕሬዚዳንት አብዲን ቤን አሊን ተክተዉ ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዚዳንት ቤጅ ሴድ ኢስቢስ በ 92 ዓመታቸዉ ባለፈዉ ሰኔ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉን ተከትሎ የፊታችን እሁድ  ቱኒዝያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ይካሄዳል። በምርጫዉ 24 ወንዶችና ሁለት ሴቶች በእጩነት መቅረባቸዉ ተመልክቶአል። 

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ