የቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መጀመር
ሰኞ፣ መስከረም 10 2008ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት ከትናንት ጀምሮ በአንድ መስመር አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ። በዚሁ ከቃሊቲ እስከ ቅዱስ ጊዮርጊስ አደባባይ በሚዘልቀው መስመር በተጀመረው አገልግሎት መደሰታቸውን ዶቼቬለ ያነጋገራቸው አብዛኛዎቹ ተጓዦች ተናግረዋል ። ሆኖም ተገልጋዮቹ አነስተኛ ያሏቸው አንዳንድ ችግሮች እንዲስተካከሉም ጠይቀዋል ።ባቡሩ ሥራ መጀመሩ የከተማይቱን የማጓጓዣ እጥረት ያቃልላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል ። የባቡር ተጓዞችን ያነጋገረው የአዲስ አበባው ወኪላችን ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ