1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ዝክር

ሐሙስ፣ ግንቦት 29 2011

ፓርቲዉ ዝክሩን አስመልክቶ ባወጣዉ መግለጫ እንዳለዉ በሁለቱ ምርጫዎች ፓርቲዉ በማሸነፉ የመንግስት ታጣቂዎች 46 አባላቱንና ደጋፊዎችን ገድለዋል፣ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ወጣቶችን አሰድደዋል።

https://p.dw.com/p/3JzU8
Professor Beyene Petros derzeitiger Vorsitzender des Oppositionsbündnisses Medrek
ምስል DW

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ መግለጫ

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ፣ ግንቦት 1992 እና ግንቦት፣ 1997 በተካሄዱት ምርጫዎች፣ ሰበብ በሀዲያና አጎራባች ዞኖች «ተገደሉ» ያላቸዉን አባላቱንና ደጋፊዎቹን ሰሞኑን ዘክሯል።ፓርቲዉ ዝክሩን አስመልክቶ ባወጣዉ መግለጫ እንዳለዉ በሁለቱ ምርጫዎች ፓርቲዉ በማሸነፉ የመንግስት ታጣቂዎች 46 አባላቱንና ደጋፊዎችን ገድለዋል፣ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ወጣቶችን አሰድደዋል።የመንግስት ፀጥታ አስከባሪዎች «ገደሏቸዉ» የተባሉትን ሰዎች ለማሰብ ባለፈዉ ግንቦት 10 ሆሳዕና ዉስጥ በተደረገዉ ስብሰባ ላይ የተካፈሉ ነዋሪዎች ለሙታኑ መታሰቢያ ሐዉልት እንዲቆም ጠይቀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጊታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ሥለ ጉዳዩ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን አነጋግሯቸዋል።

ጌታቸዉ ተድላ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ