የሶርያ ጊዜያዊ ሁኔታ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 12 2004ማስታወቂያ
ባሽር አላሳድ አገዛዝ ላይ ያተኮረ እና ለዉጥ የሚሻ መሆኑ ቢታወቅም የፕሬዝደንት አሳድ መንግስት ግን እንደቱኒዚያ፤ ግብፅና አገዛዞች በቀላሉ የሚነቃነቅ አልሆነም። በቀድሞዉ የተመድ ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን የሚመራዉ የመንግስታቱ ድርጅትና የአረብ ሊግ የሶርያ ልዩ ልዑክ ያቀረበዉ የሰላም ሃሳብም ዉጤት ሊያመጣ እንዳልቻለና ሶርያም ወደከፋ የእርስበርስ ጦርነት ልትገባ እንደምትችል እራሳቸዉ ኮፊ አናን ለመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታዉ ምክር ቤት አስታዉቀዋል። የአዉሮጳ ጥናት ማዕከል የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም የሶርያን ሁኔታ የቃኘ ዉይይት አካሂዷል። ይህ በእንዲህ እንዳለለም የአዉሮጳ ኅብረት ሶርያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ