1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶርያ ውዝግብ እና መፍትሔ ፍለጋው

ረቡዕ፣ ሐምሌ 4 2004

የተመድ የሶርያ ልዩ ልዑክ ኮፊ አናን ለሶርያ ውዝግብ መፍትሔ ለማስገኘት በተጀመረው ጥረት ኢራን እንድትሳተፍ ጠየቁ። የኢራን ተሳትፎ ዋነኛ ሚና እንደሚጫወት አናን ትናንት በቴህራን ከኢራን ባለሥልጣናት ጋ ካካሄዱት ውይይት በኋላ አስታውቀዋል። አናን መፍትሔ ለመሻት ሲሉ ባለፉት ቀናት ባካባቢው የሚገኙ ብዙ ሀገራትን ጎብኝተዋል።

https://p.dw.com/p/15VRR
epa03178156 Iranian foreign minister Ali-Akbar Salehi (R) greets UN-Arab League envoy Kofi Annan (L) in Tehran, Iran, 11 April 2012. Iran told visiting UN-Arab League envoy Kofi Annan on 11 April that Syrian President Bashar al-Assad should stay in power regardless of whatever decisions taken in the Syrian conflict. 'Iran supports the people's will in Syria for more freedom but also believes that any change should solely be done within talks between the people and the current government,' reportedly Salehi said. EPA/ABEDIN TAHERKENAREH
አናን እና ሳሊሂምስል picture-alliance/dpa

አናን ባለፈው ሰኞ በደማስቆ ከሶርያ ፕሬዚደንት በሺር አል አሳድ ጋ ከተወያዩ በኋላ ውዝግቡን ማብቃት በሚቻልበት አካሄድ ላይ ከአሳድ ጋ ስምምነት መድረሳቸውንና በዚሁ ዕቅድም ላይ የጦር መሣሪያ ከታጠቁ የተቃዋሚ ቡድኖች መሪዎች ጋ እንደሚወያዩ ያስታወቁበት ድርጊት ተስፋ መፈጠቁ ይታወሳል።
« ሁከቱን ማብቃት እንደሚያስፈልግ እና እንዴት ማስወገድ እንደሚቻልም ተወያይተናል። ውዝግቡን ማብቃት በሚቻልበት አንድ አካሄድ ላይ የተስማማን ሲሆን፡ በዚሁ ጉዳይ ላይ የጦር መሣሪያ ከታጠቀው የተቃዋሚ ወገንም ጋ እንወያይበታለን። የፖለቲካ ውይይቱን ማራመድ አስፈላጊ መሆኑንም በአፅንዖት አሳስቤአለሁ። ፕሬዚደንቱም ተስማምተዋል። »
የሶርያ መንግሥት አናን ያዘጋጁትን ባለስድስት ነጥብ የሰላም ዕቅድን እንደሚያከብርና ዓለም አቀፉ ድርጅትም ዕቅዱን እስካሁን ከታየው በተሻለ ሁኔታ በትክክል ስራ ላይ እንዲያውል መጠየቁን ኣናን አስረድተዋል። የሶርያ ተቃዋሚ ወገን ግን የአናን የደማስቆን ጉብኝት በመንቀፍ የሰላሙ ዕቅዳቸው መክሸፉን አመልክቶ፡ የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በሶርያ መንግሥት አንፃር ውሳኔ እንዲያሳልፍና አሳድ ሥልጣናቸውን በሚለቁበት ጉዳይ ላይ ድርድር እንዲጀመር ነው የጠየቀው። ይሁንና፡ አናን፡ ትናንት በተቃዋሚው ቡድን አስተያየት ተስፋ ሳይቆርጡ ከሩስያ ቀጥላ ዋነኛዋ የሶርያ ወዳጅ ወደሆነችው ኢራን   በመሄድ   ለሰላሙ ዕቅዳቸው የመንግሥቱን ድጋፍ ፍለጋ በቴህራን ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሊ አክባር ሳሌሂ ጋ ሀሳብ ተለዋውጠዋል፤ ውይይቱ የተሳካ እንደነበርም አመልክተዋል።
« በሶርያ ልዩ ልዑክ ሥልጣኔ ከሚንስትሩ እና ከመንግሥታቸው አበረታቺ መልስ እና ትብብር እንዳገኘሁ መግለጽ እፈልጋለሁ። ለሶርያ ውዝግብ መፍትሔ ለማስገኘት አብረን መስራታችንን እንድንቀጥል ፍላጎቴ ነው። »
አናን ከቴህራን ቀጥለው ወደ ኢራቅ መዲና ባግዳድ በመጓዝ የፕሬዚደንት አሳድ ደጋፊ ከሚባሉት ከኢራቅ ጠቅላይ ሚንስትር ማሊኪ ጋ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።  የኢራቅ መንግሥት ቃል አቀባይ አናን ባግዳድ ከመግባታቸው በፊትእንዳስታወቀው፡ ሀገራቸው መፍትሔ በማፈላለጉ ጥረት ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት አላት። ሩስያም ብትሆን አሁን በሶርያ መንግሥት እና በተቃዋሚዎቹ ላይ ግፊት በማሳረፍ፡ ሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች ድርድር እንዲጀምሩ ማስገደድ እንደሚያስፈልግ የሩስያ ፕሬዚደንት ፑቲን አስታውቀዋል። ሩስያ አሳድን መደገፏን እንድታቆም ለማግባባት ዛሬ ወደ ሩስያ የሄዱት የሶርያ ተቃዋሚ ብሔራዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር አብደል ባሴት ሳይዳ ጥረታቸው ሳይሳካ መቅረቱ ተሰምቷል። ይህ በዚህ እንዳለ፡ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በሶርያ ጉዳይ ላይ ለመምከር ዛሬ ስብሰባ ያካሂዳል። በሶርያ የተሰማራውና ተልዕኮ በሚቀጥለው ሣምንት የሚያበቃው 300  አባላት ያሉት የታዛቢ ቡድን ዕጣ በፀጥታ ምክር ቤቱ እጅ መሆኑን የቡድኑኃላፊ ጀነራል ሙድ አስታውቀዋል።
« ከሀምሌ ሀያ በኋላ የሚሆነውን የሚወስነው የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ነው። ግን የተመድ የሶርያ ሕዝብ የወደፊት ዕጣ አስተማማኝ ለማድረግ ያሳየው ፍላጎት ከሀምሌ ሀያም በኋላ ጠንካራ ሆኖ እንደሚቀጥል እርግጠኛ ነኝ። »

Russian Foreign Minister Sergey Lavrov gestures while speaking during the annual Brussels Forum meeting in Brussels, Saturday March 21, 2009. The Brussels Forum is a high-level meeting of the most influential North American and European political, corporate and intellectual leaders to address pressing challenges currently facing both sides of the Atlantic. (AP Photo/Virginia Mayo)
ሴርጌይ ላቭሮቭምስል AP
A leader of the Syrian National Council (SNC), Abdulbaset Sieda meets with Russian Foreign Minister Sergey Lavrov, not pictured, in Moscow, Russia, Wednesday, July 11, 2012. (Foto:Misha Japaridze/AP/dapd).
አብደል ባሴት ሳይዳምስል dapd

የንስ ቪኒንግ/አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ