የሶርያ ወቅታዊ ሁኔታ
ሰኞ፣ ሐምሌ 11 2003ማስታወቂያ
የሶሪያ ተቃዋሚ ወገን የፖሊሱን የሃይል ዕርምጃ ምክንያት በማድረግ ዳማስቆስ ውስጥ ሊካሄድ ታቅዶ በነበረ "አገር አድን" ጉባዔ ላለመሳተፍ መወሰናቸዉ አይዘነጋም። በሌላ በኩል በመቶዎች የሚቆጠሩ የሶሪያ መንግሥት ተቃዋሚዎች የአሣድን አገዛዝ በጋራ ለመጣል የሚያስችል ስልት ለመወጠን ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ቱርክ ውስጥ ተሰብስበዉ ነበር። ይሄው የኢስታምቡሉ ስብሰባ የሶሪያ ተቃውሞ ባለፈው መጋቢት ወር ከጀመረ ወዲህ በዓይነቱ ከአገሪቱ ውጭ ታላቁ መሆኑ ነው። የሶርያን ወቅታዊ ሁኔታ ነብዪ ሲራክ ከሳዉዲአረብያ ዘገባ ልኮልናል።
ነብዪ ሲራክ
አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ