የሶማልያ ፕሬዚደንትና የጠቅላይ ሚንስትራቸው ልዩነት
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 6 2001ማስታወቂያ
ጠቅላይ ሚንስትሩ ግን የፕሬዚደንቱ ውሳኔ ኢ ህገ መንግስታዊ ነው በሚል ውድቅ አድርገውታል። ፕሬዚደንት ዩሱፍ አንድ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚንስትርን ሲያሰናብቱ ኑር ሀሰን ሁሴን ሁለተኛ ጊዜ መሆናቸው ነው። ኑር ሀሰን አንድ ዓመት በፊት የተሰናበቱትን አሊ መሀመድ ጌዲ ነበር የተኩት። የጀርመን የፖለቲካና የስነ ጥበብ ተቋም ተንታኝ ወይዘሮ አኔተ ቬበር ለዶይቸ ቬለ እንዳስረዱት፡ በፕሬዚደንቱና በጠቅላይ ሚንስትራቸው መካከል የቀጠለው ንትርክ በሶማልያ የሽግግር መንግስት ስራ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳርፎዋል።