የሶማሊያ የንግድ ጉባኤ በስቶክሆልም
ረቡዕ፣ ሰኔ 4 2006ማስታወቂያ
በሶማሊያ ንግድና መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ላይ ያተኮረ ጉባኤ ስዊድን ስቶክሆልም ውስጥ ትናንት ተካሄደ ። የስዊድን መንግስትና ቢዝነስ ስዊድን የተባለው ድርጅት በጋራ ያዘጋጁት ይኽው ጉባኤ የስዊድንና የሶማሊያ መንግሥታዊና የግል ድርጅቶችን ለማገናኘት እንዲሁም ለስዊድናውያን ባለሃብቶች ስለ ሶማሊያ ተጨባጭ ሁኔታ ለማስረዳት ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑ ተመልክቷል ። በጉባኤው ላይ ከስዊድንና ከሶማሊያ የተውጣጡ 150 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል ። ጉባኤው የስዊድንና የሶማሊያ የንግድ ግንኙነት እንዲጠናከር አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ የስዊድን መንግሥት የንግድ ሚኒስትር ማስታወቃቸውን የስቶክሆልሙ ወኪላችን ቴዎድሮስ ምህረቱ ዘግቧል ።
ቴዎድሮስ ምህረቱ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ