የሶማሊያ ዓለም ዓቀፍ አገናኝ ቡድን ስብሰባ በሮም
ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 2001ማስታወቂያ
የሶማሊያ ተፋላሚ ወገኖችን ለማቀራረብና ሀገሪቱን ለማረጋጋት ጥረት በሚያደርገው የአገናኝ ቡድኑ የሁለት ቀናት ጉባኤ ላይ የሶማሊያ የሽግግር መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር አሊ ሻርማርኬ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አብዱላሂ ኦማር ተካፋይ ሲሆኑ ከኢጣልያ በኩል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንኮ ፍራቲኒ ተገኝተዋል ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሶማሊያ ልዩ ልኡክ ኡልድ አብደላ እንዲሁም የአርባ አገራት እና ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች በዚሁ ጉባኤ ላይ ተካፋይ መሆናቸውን የኢጣልያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን መግለጫ ጠቅሶ ተክለ እግዚ ገብረ የሱስ ዘግቧል ።
ተክለእዝጊ ገብረየሱስ/ሂሩት መለሰ/ሸዋዬ ለገሠ