የሶማሊያ ወንበዴዎችና የስዑዲ አረቢያ ቁጣ
ረቡዕ፣ ኅዳር 10 2001ማስታወቂያ
የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ነዳጅ ዘይት የጫነት የስዑዲ አረቢያን ግዙፍ መርከብ ማገታቸዉ የሪያድ ልዑላንን ክፉኛ ነዉ ያስቆጣል።የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ትናንት እንዳሉት የወንበዴዎቹ እርምጃ ከአሸባሪነት ጥፋት እኩል የሚታይ ክፉ ደዌ ነዉ።የባሕር ላይ ወንበዴዎቹን የሚያጠቃ በርካታ ዘመናይ አለም አቀፍ የባሕር ጦር ባካባቢዉ ሠፍሮ እገታዉ መቀጠሉ ዛሬም እንደትናንቱ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ነዉ።ነብዩ ሲራክ ከጂዳ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።