የሶማሊያ ሽግግር መንግሥት የዕርቅ ጉባዔ
ማክሰኞ፣ ጥር 22 1999ማስታወቂያ
ይሄው ዕርምጃ የአውሮፓ ሕብረት በሶማሊያ ለሚሰፍር የአፍሪቃ ሰላም አስከባሪ ሃይል ገንዘብ እንዲያቀርብ ጥርጊያ የሚከፍት ሆኖ ታይቷል። የሕብረቱ የልማት ዕርዳታ ኮሜሣር ሉዊስ ሚሼል አዲስ አበባ ውስጥ በአፍሪቃ ሕብረት መሪዎች ጉባዔ አኳያ ከአብዱላሂ ዩሱፍ ከተነጋገሩ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የሶማሊያው የዕርቅ ጉባዔ በጥቂት ሣምንታት ውስጥ ሊከፈት እንደሚችል አሰረድተዋል። ሚሼል አያይዘው እንዳሉት የአውሮፓ ሕብረት አሁን ለሰላም ተልዕኮው 19 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ለማቅረብ ዝግጁ ነው። የአፍሪቃ ሕብረት መንግሥታት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ ይጠናቀቃል።