የሶማሊያ ሰብዓዊ ቀውስ
ዓርብ፣ ጥቅምት 22 2000ማስታወቂያ
በሰሞኑ የሶማሊያ መዲና መቅዲሾ ውጊያ ምክንያት በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ ። ድርጅቱ ትናንት ይፋ እንዳደረገው በሰሞኑ ውጊያ የተፈናቀሉት ሶማሊያውያን ቁጥር ሰማንያ ስምንት ሺህ ይደርሳል ። ቀድሞ በተፈናቀለው ላይ የተጨመረውን የአሁኑን ተፈናቃይ ለመርዳት የዕርዳት ድርጅቶች የበኩላቸውን እየጣሩ ነው ። ሆኖም በሶማሊያ የሚንቀሳቀሱ የተባበሩት መንግስታትም ሆነ ሌሎች የረድኤት ድርጅቶች የሚገባቸውን ያህል ችግር ላይ ለወደቀው ህዝብ መድረስ አልቻሉም ። ለዚህም የኦቻ ሶማሊያ ሀላፊ ለተፋላሚ ወገኖች ጥሪ አድርገዋል ።