የሶማሊያው የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት
ዓርብ፣ ኅዳር 25 2002ማስታወቂያ
ጥቃቱ ካወገዙት ውስጥ የተበባሩት መንግስት ድርጅት የአውሮፓ ህብረት የአፍሪቃ ህብረት የአረብሊግ እንዲሁም ዩናይትድ ስቴትስ ይገኙበታል ። አዲሱ የሶማሊያ የሽግግር መንግስት ስልጣን ከያዘ ወዲህ በሀገሪቱ ከደረሱት ጥቃቶች ዓለም ዓቀፍ ትኩረት የሳበውን የትናንቱን አደጋ በሶማሊያ ተመሳሳይ ጥቃቶችን የሚያደርሰው አልሸባብ አልፈፀምኩም ሲል አስተባብሏል ። የግጭቶችን መንስኤ እና መፍትሄያቸውን የሚያጠናው የክራይስ ግሩፕ ባልደረባ ረሺድ አብዲ ለዶይቼቬለ በሰጡት አስተያየት ጥቃቱ አድራሹ አልሸባብ መሆኑ ግልፅ ነው ይላሉ ።
ሂሩት መለሰ /ሸዋዬ ለገሠ