1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስደት መንስኤን የመረመረዉ ጉባኤ በዘሄግ

ረቡዕ፣ የካቲት 21 2010

በአፍሪቃ ቀንድ ሃገራት ለስደት የሚዳረጉትን ምክንያቶች እና ሕገወጥ የሰዉ አዘዋዋሪዎችን በሚመለከት የተደረጉ ጥናቶች ዉጤት የቀረበበት ትናንት ስብሰባ በዘሄግ ኔዘርላንድስ ተካሄደ። ጥናቱን ያደረገዉ እና ስብሰባዉንም ያዘጋጀው በኔዘርላንድስ የቲልቡርግ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን የመቀሌ እና በኬንያ የታንግዛ ዩኒቨርሲቲዎችም የጥናቱ ተሳታፊዎች ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/2tTX8
Mittelmmeer gerettete afrikanische Flüchtlinge
ምስል picture-alliance/AP/E. Morenatti

ጥናቱ የተዘጋጀዉ በኔዘርላንድ፣ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ዩኒቨርሲቲዎች ትብብር ነዉ

 በስብሰባዉ ተመራማሪዎች የመንግሥት እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል። ለስደት እና ፍልሰት ምክንያት የሆኑ ዉስጣዊ እና ዉጫዊ ምክንያቶች፤ የድንበር ፖለቲካ በስደት እና ፍልሰት ላይ ስላለዉ ተጽዕኖ፤ በስደተኞች ላይ የሚደርስ የአዕምሮ ጭንቀት፤ በስደተኞች እና በዉሳኔያቸዉ ላይ እንዲሁም በራሱ በራሱ በፍልሰት እና ስደት ቀጣይነት እና ስላለው የሚያስረዱ ጥናቶች ቀርበዋል። ከብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ