1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የስንዝሮ አባት»የፈጠራ ባለሞያዉ

እሑድ፣ መጋቢት 23 2010

ስንቶቻችን ነን የአለቃ ገብረሃናን ተረቶች የስንዝሮን ታሪክ በተረት መልክ ስንሰማ ያደግን? በሀገራችን ትልቅ ቦታ የሚሰጠዉ ተረት የአንድ ማህበረሰብን ብስለት፣ አኗኗር ፣መስተጋብርና አመለካክት የማሳየት አቅም ያለዉ ምናባዊ ትረካ ነዉ። በልጅነት ስለአለቃ ገብረሃና ስለስንዝሮ በተረት መልክ እየሰማን ያደግን ኢትዮጵያዉያን ጥቂቶች አይደለንም።

https://p.dw.com/p/2vIKj
Äthiopien Girma Zeleke
ምስል Gebru God

ስንዝሮን በጥበብ ያንቀሳቀሱት የፈጠራ ሰው አቶ ግርማ ዘለቀ

በአብዛኞች ኢትዮጵያዉያን አዕምሮ ተቀርጾ ያለው በቀደምት ጊዜያቶች የልጅነት መማሪያ መጽሐፎቻችን ላይ የምናስታውሰውን ስንዝሮን በተንቀሳቃሽ ፊልም «በአኒሜሽን» በመስራት በቴሌቪዢን መስኮት ሕይወት ሰጥተዉ እስክስታን አስችለዉ ብሎም ስንዝሮን በማየት በመዳሰስ እንደ ልጅነታችን እኛም ለልጅ ልጆቻችን የስንዝሮን ተረት እንድንተርክ ከኢትዮጵያ ዉጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያንም  አማርኛ ቋንቋ እንዲማሩ በማዝናናት እንዲገለግል በአሻንጉሊት መልክ ያበረከቱት አቶ ግርማ ዘለቀ አልያም ግርማ ስንዝሮ የስንዝሮ አባት፤ስንዝሮን ለትዉልድ ማስተላለፋቸዉ እንደ አብዛኞቻችን ስንዝሮ በልጅነት አዕምሮዋቸዉ ያሳደረዉ ጥሩና ጥልቅ ትዝታ በመኖሩ እንደሁ እሙን ነዉ። ባለፉት ሳምንታት  የአቶ ግርማ ዘለቀ ድንገተኛ ሞት እና አሟሟት ብዙዎችን አሳዝኖአል።  አቶ ግርማ ዘለቀ ስንዝሮን  ብቻ ሳይሆን ከልጅነታቸው ጀምሮ ልዩ ተሰጥኦ የነበራቸው በመሆኑ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን በማቅረብ መታዎቅ የጀመሩት ከትምህርትት ቤት ከልጅነት እድሜያቸው ጀምሮ እንደነበር ታሪካቸዉ ያሳያል።  አቶ ግርማ ዘለቀን በተለያዩ የፈጠራ ስራዎቻቸዉ በቅርብ የሚያዉቋቸዉ የኢትዮጵያ የአምራቾች የግል ኢንዱስትሪዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሳሉ እንደሆን የነገሩን እና አሁን ግን ስደተኛ ነኝ ያሉን በሰሜን አሜሪካ ነዋሪ የሆኑት አቶ ብርሃነ መዋ ናቸዉ። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመጫዉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ