የ«ሳይክስ ፒኮት» ውል መቶኛ ዓመት
ረቡዕ፣ ግንቦት 3 2008ማስታወቂያ
ፈረንሳይና ብሪታንያ መካከለኛው ምሥራቅን ለሁለት የተቀራመቱበት ስምምነት ዘንድሮ አንድ መቶ አመት ደፈነ ። ሥምምነቱን በተፈራረሙት በሁለቱ ሐገራት ባለሥልጣናት «ሳይክስ ፒኮት» ተብሎ የሚጠራዉ ዉል በአንደኛው የዓለም ጦርነት መሀል እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር በ1916 የተደረገ ነበር። ሁለቱ የአዉሮጳ ሐያላን በጦርነቱ ከተዳከመችዉ ከኦስማን ቱርክ የሚቀሙትን የመካከለኛዉ ምሥራቅን ግዛት በሚስጥር የተከፋፈሉበት ስምምነት ነው።የኬርስተን ክኒፕን ዘገባ የበርሊኑ ወኪላችን አጠናቅሮታል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ