የሳውዲ የምሕረት አዋጅ እና በዚያ አለፈቃድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን
እሑድ፣ ሚያዝያ 15 2009ማስታወቂያ
በዚያን ጊዜ በሳውዲ ይገኙ የነበሩ ብዙ ኢትዮጵያዉያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የፈለጉ ሁሉ ሳይቀሩ ታድያ ትልቅ ችግር ገጥሟቸው ነበር፣ ታስረዋል፣ ተንገላተዋል። የሳውዲ መንግሥት አሁን ከአራት ዓመት በኋላም በጎርጎርዮሳውያኑ የዘመን ቀመር ባለፈው መጋቢት (29/03/2017) ተመሳሳይ የምሕረት አዋጅ አውጥቷል። ይኸው የሳውዲ መንግሥት የምሕረት አዋጅ ለዘጠና ቀናት የሚቆይ ነው። ሳውዲ ዐረቢያ «ከሕገወጥነት የነጻች ሀገር» የሚል መጠሪያ የሰጠችው የምሕረት አዋጅ አንድ ወር ሊሆነው ጥቂት ቀናት ነው የቀሩት።
ከ37 ሚልዮኑ የሳውዲ ሕዝብ መካከል ሁለቱ ሚልዮን በሕገ ወጥ እንደሚኖር መዘርዝሮች ያሳያሉ። በሳዑዲ በሕገወጥነት ይኖራሉ ከሚባሉት የውጭ ዜጎች መካከል ኢትዮጵያውያንም ይገኙባቸዋል። ኢትዮጵያውያኑ በምሕረት አዋጁ በቀረበላቸው እድል እንዲጠቀሙበት በተደጋጋሚ ማስገንዘቢያ እየቀረበ ነው። በዚሁ አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ውይይት አካሂደናል።
አርያም ተክሌ
ማንተጋፍቶት ስለሺ