1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሳምንቱ የስፖርት ጥንቅር

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 17 2010

ትናንት የ92 አመቷ የእንግሊዝ ንግሥት ያስጀመሩት የለንደን ማራቶን ሲጠናቀቅ በሁለቱም ፆታ ኬንያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል።  በሴቶች  የ 34 አመትዋ ኬንያዊት ቪቪያን ቼሪዮት የለንደንን ማራቶን 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ በማጠናቀቅ አዲስ የራስዋን ምርጥ ሰአት በማስመዝገብ አሽንፋለች ።

https://p.dw.com/p/2wX33
UK äthiopische Athleten beim London-Marathon
ምስል DW/H. Demisse

ስፖርት ሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ.ም.

የሴቶች ማራቶን ትናንት ሲጀመር ከ15 አመት በፊት በ2003  በ ፓላ ራድክሊፍ የተመዘገበው የርቀቱ ሰዓት 2ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ ይሻሻላል የሚል እምነት ነበር ። ለዚህም ያግዝ ዘንድ የወንድ አሯሯጭ ተካቶ ውድድሩ ሲካሂድ ባለፈው አመት ባደረጉት ውድድር 2 ሰዓት ከ17 ከ01ሰከንድ ያላት ሜሪ ኪታኔ እና 2 ሰዓት ከ17ደቂቃ ከ56 ሰከንድ ምርጥ ሰዓት ያላት ጥሩነሽ ዲባባ አዲስ ሰዓት ያስመዘግባሉ ከተባሉት ቀዳሚዎች ነበሩ።  እስከ16 ኪሎሚትር ድርስ ውድድሩ እንደታቀደለት የሚሄድ ይመስሰል ነበር። በተለይ ሜሪ ኪታኔ ጥሩንሽን አምልጣ ለመውጣት ስትሮጥ ፍጥነትዋ በግማሽ ደቂቃ ክፖላ ራድክሊፍ በልጦ ነበር።  ውድድሩን በቀዳሚነት እየመራች ይሻሻላል ከተባለው ሰዓት መራቅ ጀመረች። 28ኛው ኪሎ ሜትር ላይ ስትድርስ ጭርሱን መዘግየት ጀመረች ፥ በውድድሩ ጥቁር እና ነጭ መስመር ያለው መለያ ለብሰው የነበሩት  አሯሯጮቹ የታስበውን ያህል ውድድሩን ማፍጠን አልቻሉም ። ሙቀቱ ያቀልጥ በነበረው የለንደን አየር ጥሩነሽ ውድድሩን ትመራው ከነበረው ሜሪ ኪታኔ ጋር የነበራትን 52 ሰከንድ ልዮነት በ8 ሰከንድ አጥብባው አፍታም ሳትቆይ  30ኛው ኪሎ ሜትር ላይ ጥላው ወጣች። ሶስተኛ የነበረችው ቪቪያን ቼሪዮት ከ33ኛው ኪሎ ሜትር ቀዳሚነቱን ተረክባ ገሰገሰች። በአስደንጋጭ ፍጥነት ውድድሩን ይመሩት የነበሩት አትሌቶች አቅማቸውን ጨርሰው ከውድድር ሲወጡ እና ወደኋላ ሲቀሩ በዝግታ የጀመሩት አሸናፊዋች ሆኑ ። ሙሉዉን ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ፤

UK äthiopische Athleten beim London-Marathon
ምስል DW/H. Demisse

 

ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ