የሱዳን ጉባዔ በዋሽንግተን17 ሰኔ 2001ረቡዕ፣ ሰኔ 17 2001በሰሜን እና በደቡብ ሱዳን መካከል ከአራት ዓመት በፊት የተፈረመውን የሰላም ውል ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማስደረግ የሚረዳ አንድ ትልቅ ጉባዔ በትናንትናው ዕለት በዋሽንግተን ተካሄደ።https://p.dw.com/p/IYCxዚ,ሰላሙ ውል ከአራት ዓመት በፊት በተፈረመበተ ጊዜምስል APማስታወቂያየዩኤስ አሜሪካ መስተዳድር ለሱዳን ችግር ዘላቂ መፍትሄ ለማስገኘት ሁሉም የሚመለከታቸው ወገኖች የየበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጠይቆዋል። በዚሁ የደቡብ የሱዳን ህዝብ እንቅስቃሴና የሰሜኑ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ በዋነኛ ታዳሚነት በተጋበዙበትና ትልቅ ግምት በተሰጠው ጉባዔ ላይ የሰላሳ ሁለት ሀገሮችና ድርጅቶች ተወካዮች ተሳታፊዎች ነበሩ። አበበ ፈለቀ/አርያም ተክሌ ሂሩት መለሰ AFA/AA