የሱዳን ቀውስ እና የቀጠናው ፖለቲካ
ሰኞ፣ ሰኔ 10 2011ማስታወቂያ
የሱዳን የቀድሞ ፕሬዝዳን ኦማር ሐሰን አል-በሽር ከስልጣን ገለል ቢሉም ይመሩት የነበረው ሥርዓት አሁንም እንዳለ ነው። አገሪቱን የሚያስተዳድረው ወታደራዊ ምክር ቤት ሥልጣኑን ለሲቪል መንግሥት እንዲያስረክብ የሚሹት የአገሪቱ ተቃዋሚዎች መከፋፈል ቀውሱ እንዲህ በቀላል መፍትሔ ለምግኘቱ አጠራጣሪ አድርጎታል። የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች፤ የአፍሪካ ኅብረት እና ኢትዮጵያን ጨምሮ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በየራሳቸው መንገድ ለሱዳን ፖለቲካዊ ቀውስ መፍትሔ እያፈላለጉ ነው።በሱዳን የሚኖር የኃይል አሰላለፍ ለውጥ በኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ አገራት ላይ ምን አይነት ተፅዕኖ ያሳድራል? በዛሬው የማኅደረ ዜና መሰናዶ ገበያው ንጉሴ የሚመለከተው ጉዳይ ነው።
ገበያው ንጉሴ
እሸቴ በቀለ