የሱዳንና የኢትዮጵያ መሪዎች ዉይይት
ማክሰኞ፣ መጋቢት 26 2009ማስታወቂያ
ኢትዮጵያን ከሱዳን የባሕር ወደብ ፖርት ሱዳን ጋር የሚያገናኝ የባቡር ሐዲድ ለመዘርጋት ሁለቱ መንግሥታት መስማማታቸዉን የሁለቱ ሐገራት መሪዎች አስታወቁ።ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ የተነጋገሩት የሱዳኑ ፕሬዝደንት ዑመር ሐሰን አል በሽር እና የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ በጋራ እንዳስታወቁት ሱዳን፤ ሐዲዱ የሚዘረጋበትን መሬት ፈቅዳለች። በሁለቱ ሐገራት መካከል ነፃ የንግድና የምጣኔ ሐብት ቀጠና ለመመስረት ማቀዳቸዉንም መሪዎቹ አስታዉቀዋል። የሁለቱን መሪዎች ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለዉ ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስን
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ