የሰብአዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ
ረቡዕ፣ ሰኔ 1 2008ማስታወቂያ
ሥለ ሠብአዊ መብት ይዘት ከወደ አዲስ አበባም ጥሩ ነገር አይሰማም። የሠብአዊ መብት ጉባኤ (ሠመጉ) ባወጣዉ ልዩ መግለጫ የወልቃይት፤ የቅማንት፤የቁጫ እና የኮንቶማ ማሕበረሰብ አባላት መብታቸዉ እንዲከበር በመጠየቃቸዉ ተገድለዋል፤ ደብዛቸዉ ጠፍቷል፤ ታፍነዋል ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋልም ይላል።ጉባኤዉ በ21 ገፅ ባጠናቀረዉ ዘገባዉ እንደዘረዘረዉ አራቱም ማሕበረሰቦች ያቀረቡት ጥያቄ ተመሳሳይ እና በሕገ-መንግሥቱ የተደነገገላቸዉ የማንነት ጥያቄ ነዉ።የተፈፀመባቸዉ በደል ግን ከፍተኛ ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሰ