የሰመጉና የኢሕባሴማ የፍርድ ቤት ዉሎ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 7 2005ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የፌደራል ሠበር ሠሚ ችሎት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤና የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማሕበር ባቀረቡት ይግባኝ ላይ የመጨረሻ ብይን ለመስጠት ለፊታችን አርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሠጠ።የኢትዮጵያ መንግሥት የዛሬ ሰወስት ዓመት ግድም ለበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማሕበራት አዲስ ባፀደቀዉ ደንብ መሠረት ሁለቱ ተቋማት በድምሩ ከአስራ-ስድስት ሚሊዮን በላይ ብር ታግዶባቸዋል።ማሕበራቱ ገንዘቡ እንዲለቀቅላቸዉ እየተሟገቱ ነዉ።ችሎቱ ከዚሕ ቀደም ዛሬ የመጨረሻ ብይን እንደሚሰጥ አስታዉቆ ነበር።ዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ ለመስጠት የወሰነዉ ግን በተለይ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማሕበር ጉዳዩን በድርድር ለመፍታት መጠየቁን በማስታወቁ ነዉ።ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ካዲስ አበባ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ