የሰላም የኖቤል ሽልማት የሕጻናት ጉዳይ ተቆርቋሪዎች
ዓርብ፣ መስከረም 30 2007«የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ የ2014 የኖቤል የሰላም ሽልማት ስለወጣቶችና ሕጻናት ጭቆናና የሕጻናት የትምህርት መብት ለታገሉት ለካይላሽ ሳታይራቲ እና ማላላ ይሱፍዛይ እንዲሰጥ ወስኗል። ሕጻናት ወደትምህርት ቤት መሄድ አለባቸው። ለገንዘብ ማግኛ ሲባል ሊበዘበዙ አይገባም።»
ወጣት ሴቶች የትምህርት እድል እንዲያገኙ ከፍተኛ ትግል በማካሄድዋ የምትታወቀዉ የ17 ዓመትዋ ፓኪስታናዊት ማላላ በጎርጎሮሳዊዉ 2012 ዓ,ም ከጽንፈኛዉ ታሊባን ቡድን በደረሰባት ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ላይ መዉደቅዋ ይታወሳል። ሌላዉ የዘንድሮ የሰላም ኖቤል ተሸላሚ የ60 ዓመቱ ህንዳዊ ካይላሽ ሳትያርቲ፤ የጋንዲን ትልቅ የመነሳሳት ኃይል መርሃቸዉ በማድረግ በሕጻናት ላይ የሚደረገዉን የጉልበት ብዝበዛ በመቃወም በርካታ የተቃዉሞና ሰላማዊ ሰልፎችን በማነሳሳታቸዉ ይታወቃሉ። 900 ሽህ ይሮ ሽልማትን እንደያዘ የተነገረለት የሰላም ኖቤል ሽልማት የፊታችን ታህሳስ 10፣ 2014 ዓ,ም ኖርዌ ስቶክሆልም ላይ ይሰጣል።
በሌላ በኩል ትናንት ሃሙስ ፈረንሳዊው ደራሲ ፓትሪክ ሞዲያኖ የ2014 ዓም የሥነ ጽሑፍ የኖቤል አሸናፊ መሆናቸው ተገለጸ። ስቶክሆልም የሚገኘው የስዊድኑ የካሮሊንስካ ተቋም እንዳስታወቀው፣ እስከዛሬ 30 መጽሓፍት ያወጡት የ69 ዓመቱ ሞዲያኖ የሰዎችን አስደማሚ እጣ የማቅረብ ልዩ ችሎታቸለአሸናፊነት አብቅቷቸዋል። ሞዲያኖይህንኑ880,000 ዩሮ የያዘውን እና እአአየፊታችን ታህሳስ 10፣ 2014 ዓም በስቶክሆልም የሚሰጠውን ሽልማት ያገኙ 15ኛው ፈረንሳዊ ደራሲ ናቸው።
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሰ