የሰለጠነ የሰው ኃይል ዕጥረት በጀርመን
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 4 2002ማስታወቂያ
የስራ አጡ ቁጥር ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ወቅት ላይ ከአሁን ወዲያ በተለይ ልዩ ሙያ ያላቸው ሰራተኞች ዕጥረት ይኖራል የሚል ግምት አልነበረም ። ይሁንና ዕውነታው ግን ከዚህ የተለየ ሆኗል ። በአብዛኛዎቹ የአውሮፓ ኢንዱስትሪዎች ባላቀ ደረጃ የሰለጠኑ ባለሞያዎች ዕጥረት አሁንም ትልቅ ራስ ምታት እንደሆነ የዘለቀ ጉዳይ ነው ። እስካሁን መፍትሄ ተብለው የተወሰዱት ዕርምጃዎችም የዶይቼቬለው ዲርክ ካውፍማን እንደዘገበው በጀርመንም ጭምር ለውጥ አላስገኙም ። የዛሬው አውሮፓ ጀርመን የሚያተኩርበት ርዕሰ ጉዳይ ነው ።
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ