የርዳታ ጥሪ ለቻድ ሃይቅ አዋሳኝ ሃገሮች
ሐሙስ፣ ግንቦት 18 2008ማስታወቂያ
ከዉኃዉ ማነስ በተጨማሪ ባካባቢዉ የሚካሔደዉ ግጭት የነዋሪዎቹን ጭግር ማባባሱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታዉቋል። ጽንፈኛዉ ቡድን ቦኮሃራም ባለፉት ሰባት ዓመታት በቻድ ሃይቅ አዋሳኝ ሃገራት 15 ሺህ ሰዎችን መግደሉ ተዘግቦአል። የቻድ ሃይቅ አዋሳኝ ሃገራት መካከል የሚታየዉ ችግር በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ችላ ተብሎአል በሚል ከፍተኛ ቅሪታ ቀርቦአል። በያዝነዉ ሳምንት ኢስታንቡል-ቱርክ በተሠየመዉ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ የቻይድ ሃይቅ አዋሳኝ ሃገራት ችግርና ረሃብ ተነስቶ ነበር። የቻይድ ሃይቅ አዋሳኝ ሃገራት ችግርና ረሃብ ጉዳይ ናይሮቢ ኬንያ የሚገኘዉን ወኪላችንን በስልክ አነጋግረነዉ ነበር።
ፋሲል ግርማ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ