የርዋንዳ እና የጀርመን ግንኙነት2 የካቲት 2005ቅዳሜ፣ የካቲት 2 2005ርዋንዳ እንደገና ከጀርመን የገንዘብ ርዳታ እንደምታገኝ ተገለጸ። የጀርመን የልማት ተራድዖ ሚንስቴር ባለፈው ሣምንት በበርሊን ከርዋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሉዊዝ ሙሽኪዋቦ ጋ ሀሳብ ከተለዋወጠ በኋላ እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱን አመልክቶዋል።https://p.dw.com/p/17bC0ምስል Fotolia/ThinManማስታወቂያ አንድ የተመድ የጠበብት ቡድን ርዋንዳ በምሥራቃዊ ዴሞክራሲያዊ ኮንጎ ሬፓብሊክ በመንግሥቱ አንፃር የሚዋጉትን ራሱን « ኤም 23 ብሎ የሚጠራው ቡድን ዓማፅያንን እንደምትረዳ ያስታወቀበትን ትናት ይፋ ካደረገ በኋላ የጀርመን መንግሥት ለርዋንዳ ይሰጠው የነበረውን ሰባት ሚልዮን ዩሮ የበጀት ርዳታ ማቋረጡ ይታወሳል። ፊሊፕ ዛንደር/አርያም ተክሌ