የሪቻርድ ሆልብሩክ ዜና ዕረፍት
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 5 2003ማስታወቂያ
የዩኤስ አስተዳደር ባለስልጣናት እንዳስታወቁት፡ ሆልብሩክ ያረፉት ሀኪሞች የተሰነጠቀውን የደም ባምቧ ለመጠገን የሀያ ሰዓት የቀዶ ጥገና ካደረጉላቸው ከጥቂት ቀናት በኋላ ነበር። የስድሳ ዘጠኝ ዓመቱ ሆልብሩክ ባለፈው ዓርብ ድንገት ህሊናቸውን በሳቱ ጊዜ ነበር ወደ ሀኪም ቤት የተወሰዱት። የስድሳ ዘጠኝ ዓመቱ ሪቻርድ ሆልብሩክ ከአራት አሰርተ ዓመት በላይ በዲፕሎማቲክ ሙያ ያገለገሉ ፖለቲከኛ ነበሩ፤ አከራካሪ የነበሩት ዲፕሎማት በተለይ የሚታወቁት ሶስት ዓመት የቆየውን የቦዝንያ የርስ በርስ ጦርነት ያበቃውን የዴይተን የሰላም ውል በማደራደራቸው ነው።
ዛቢን ሚውለር
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ