1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሥዕል ጥበበኛው ብሩክ

ዓርብ፣ ግንቦት 2 2011

ከልጅነት ዕድሜው ሥዕልን መሳል የጀመረው ወጣት ሠዓሊ ብሩክ የሽጥላ፤ ጥንካሬና ብርታቱን ሰንቆ በትዕግስት አሁን ያለበት ደረጃ መድረሱን ይናገራል። ያለፈ ሕይወቱን ተመርኩዞ ለሌሎች እንዲረዳ በማሰብ መጽሐፍ ጽፏል።

https://p.dw.com/p/3IHQP
Äthiopischer Künstler Biruk Yeshetila
ምስል privat

ሠዓሊ ብሩክ የሽጥላ

የሥዕል ጥበብን በልጅነት ዕድሜው ከእናቱ በመጣለት ስጦታ መስራት እንደጀመረ ይናገራል፤ ብሩክ የሽጥላ። ሙሉ ጤነኛ ሆኖ የተወለደው ብሩክ በ12 ዓመቱ በድንገት በግራ እግሩ ላይ ህመም ይሰማዋል። ህመሙ እየቆየ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ ይጀምራል። በወቅቱ ህክምናዎችን ቢያደርግም ሊሻለው ግን አልቻለም። ብሩክ የተለያየ የህክምና ዓይነቶችን እንዳደረገ ይገልጻል። «ሙሉ በሙሉ መንቀሳቀስ አልችልም ነበር። የአጥንት ስፔሻሊስት የተለያዩ የህክምና ባለሙያዎች ጋር ከፍተኛ የሆነ ህክምና አድርገን ነበር። » በወቅቱ ምንም መፍትሄ ሊገኝ አልቻለም። በሽታውም እየባሰ ሄደ። በለጋ ዕድሜው የአልጋ ቁራኛ ሆነ። በወቅቱ ህይወቱን ከባድ እንዳደረገበት ይናገራል። «ከፍተኛ የሆነ ድብርትና ጭንቀት ከቶኝ፤ መጥፎ ስሜቶች እንዲሰሙኝ አድርጎኝ ነበር።» ብሩክ በድብርትና በጭንቀት ውስጥ የነበረ ህይወቱን የሚለውጥ አጋጣሚ ተከሰተ። ህይወትን የሚያነቃቁ የሚላቸውን መጽሀፍቶች በማንበብ የህይወቱን ለውጥ መንገዱን ጠረጉለት። «አነባቸው የነበሩ መጽሐፍቶች ህይወትን ሊቀይሩ የሚችሉ ነበሩ። የሌሎች ሰዎችን የህይወት ተሞክሮዎችን የያዙ ግለታሪኮች እንዲሁም አነቃቂ መጽሐፍቶች እና መንፈሳዊ መጽሐፍቶች በወቅቱ አነብ ነበር።» ብሩክ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ወዳቆመው ስዕል ስራውን ጀመረ። ሆኖም ሌላ ህልሙን እውን ሊያደርግለት የሚችል አጋጣሚ በድጋሜ ተከሰተ። ከዚህ ቀደም ህክምናው በሀገር ውስጥ ሊኖር እንደማይችል የተነገረው ቢሆንም፤ ቆሞ ሊራመድ የሚያስችለው አጋጣሚ፤ ከ14 ዓመት በሃላ ባላሰበውና ባልጠበቀው፤ ያን ወቅት በትውስታ ትልቅ እድል ነበር ይላል። «ይህ ለእኔ ትልቅ ዕድል ነበር። ምክንያቱም ከ14 ዓመት በሃላ ነበር ይሄ ዕድል ተፈጠረልኝ እና መራመድ ቻልኩ።» የኔ ስጦታ የሚል መጽሀፍ ጽፏል። መጽሀፉን ለመጻፍ ያነሳሳው በተስፋ መቁረጥ ውስጥ የወጣትነት የህይወቱ እንደእኩዮቹ አለማሳለፉን፤ ሰዓሊ ብሩክ ያስታውሳል። ብሩክ ሊያረጋጋው ፤ በጨለመ ህይወቱ ጭላንጭል ተስፋ የሚሰጠው አቶ እንደነበር ይናገራል። ሙሉው ዝግጅት ማገናኛው ላይ ይገኛል


ነጃት ኢብራሂም
እሸቴ በቀለ 

Äthiopischer Künstler Biruk Yeshetila
ምስል privat