የሞሪታንያ ፕሬዚደንት ተተኩሶባቸው ቆሰሉ
እሑድ፣ ጥቅምት 4 2005ማስታወቂያ
በዚያ ከተደረገላቸው ቀዶ ጥገና በኋላ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ፕሬዚደንቱ ለሕዝባቸው ከፓሪስ ሐኪም ቤት አልጋቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሬዚደንት አብደል አዚዝ የደረሰባቸው የመቁሰል አደጋ ለሕይወታቸው አስጊ አለመሆኑን የሀገሪቱ መገናኛ ሚንስትርም በቴሌቪዥን ገልጸዋል። ሚንስትሩ አክለው እንዳስረዱት፡ የሞሪታንያ ክብር ዘብ በስህተት በፕሬዚደንታዊው የተሽከርካሪዎች አጀብ ላይ ተኩሶዋል። ይሁንና፡ አደጋውን በተመለከተ የተለያየ ታሪክ ስለሚሰማ የሆነውን በትክክል ማወቁ በወቅቱ አዳጋች መሆኑን ተያይዞ የደረሰን ዘገባ አስታውቋል። ቀደም ሲል አንድ ስማቸው ያልተገለጸ የጦር መኮንን በሰጡት መግለጫ ፕሬዚደንቱ በአንድ በሞተር ባይስክል ይጓዝ በነበረ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በሰሜናዊ ኑዋክሾት እንደተተኮሰባቸው አስታውቀዋል።
አርያም ተክሌ
ልደት አበበ