የምግብ እጥረትና የጀርመን እቅድ
ዓርብ፣ የካቲት 27 2001ማስታወቂያ
የሐገሪቱ ምክር ቤት ትናንት በተነጋገረበት እቅድ መሠረት አብዛኛዉ የአፍሪቃ በጥቂቱ ደግሞ የእስያ ሐገራትን የገጠር ልማት ለማገዝ ጀርመን በአመት የስድስት መቶ ሚሊዮን ዩሮ ርዳታ ትሰጣለች።ይሕ የገንዘብ መጠን የጀርመን የልማት ተራድኦ ሚኒስቴር ከሚያወጣዉ አመታዊ በጀት አስር በመቶ ያሕል መሆኑ ነዉ።የሐሳቡ ደጋፊዎች እንደሚሉት እቅዱ ድሕነትንና ረሐብን ለመቀነስ፥ የለጋሽ ሐገሮችን አሰራርም ለመለወጥ ይረዳል።