የምክርቤት ምርጫ በጀርመን14 ጥር 2001ሐሙስ፣ ጥር 14 2001የጎርጎሮሳውያኑ 2009 ዓመተ ምህረት በጀርመን በርከት ያሉ ዐበይት ምርጫዎች የሚካሄዱበት ዓመት ነው ።https://p.dw.com/p/GeQQሮላንድ ኮኽምስል APማስታወቂያ በ2009 የአንዳንድ ፌደራል ክፍላተ ሀገራት ፣ እንዲሁም አጠቃላይ ምርጫ የሚካሄድ ሲሆን ፤ በዚሁ ዓመት ህዝቡ ለአውሮፓ ፓርላማ ዕንደራሴዎችም ድምፅ ይሰጣል ። በፌደራዊ ክፍለ ሀገር ደረጃ ለ2009 ከታቀዱት ምርጫዎች አንዱ ዋነኛውን የጀርመን የንግድ ማዕከል ፍራንክፈርትን በሚያጠቃልለው በሄሰን ፌደራዊ ክፍለ ሀገር ባለፈው ዕሁድ የተካሄደው ምክርቤታዊ ምርጫ ነው ።