የምሥራቅ አፍሪቃ ታዋቂ አትሌቶች አሰልጣኝ ተጠርጥሮ መታሰር14 ሰኔ 2008ማክሰኞ፣ ሰኔ 14 2008የአትሌቶች አሰልጣኝ ጃማ ኤደን በስጳኝ የባርሰሎና ከተማ አቅራቢያ ባረፉበት ሆቴል ትናንት በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሶማልያዊው አሰልጣኝ የታሰሩት የስጳኝ ፖሊስ በክፍላቸው ድንገተኛ ፍተሻ ካደረገ እና የተከለከሉ የደም ሴሎችን የሚጨምር ንጥረ ነገር፣ እንዲሁም ፣ ወደ 60 የሚጠጉ መርፌዎች ካገኘባቸው በኋላ ነው።https://p.dw.com/p/1JAmwምስል picture-alliance/dpa/G. Breloerማስታወቂያ[No title]To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 audio በወቅቱ ስድስት የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ሀኪሞች እና የስጳኝ ፀረ ጉልበት ሰጪ ንጥረነገር ተቋም በጋራ ለስልጠና ከአሰልጣኝ ጃማ ኤደን ጋር የተገኙትን ከ25 የሚበልጡ አትሌቶችን የደም ናሙና ለምርመራ ወስደዋል። ሃይማኖት ጥሩነህ አዜብ ታደሰ