1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምሥራቅ አፍሪቃ ማኅበረሰብ ስብሰባ በአሩሻ

ዓርብ፣ የካቲት 25 2008

የምሥራቅ አፍሪቃ ማኅበረሰብ በእንግሊዝኛ ምኅፃሩ (EAC) ትናንት አሩሻ ታንዛኒያ ውስጥ ባከናወነው ስብሰባ ደቡብ ሱዳንን በአዲስ አባልነት ሲቀበል፤ የቡሩንዲ ቀውስን ለመፍታት ያስችል ዘንድ አዲስ አደራዳሪ ሾሞዋል።

https://p.dw.com/p/1I6tf
East African Community Gipfel Tansania Arusha
ምስል picture-alliance/dpa/Xinhua

[No title]

በጦርነት የተዳቀቀችው ደቡብ ሱዳን የምሥራቅ አፍሪቃ ማኅበረሰብ በእንግሊዝኛ ምኅፃሩ (EAC) ቡድንን እንደተቀላቀለች ይፋ ያደረጉት የወቅቱ የምሥራቅ አፍሪቃ ማኅበረሰብ ሊቀመንበር የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ናቸው። ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ የንግድ ማኅበረሰቡ በአሁኑ ወቅት 150 ሚሊዮን ሰዎችን ያካትታል ተብሏል። ይኽ በእንዲህ እንዳለ የቀድሞው የታንዛኒያ ፕሬዚ ዳንት ቤንጃሚን ምካባ የቡሩንዲ ቀውስን እንዲያደራድሩ በንግድ ማኅበረሰቡ ተሹመዋል። የ77 ዓመቱ አዲስ አደራዳሪ የቡሩንዲ ቀውስ እልባት እንዲያገኝ በአዲስ መልክ ጥረት እንደሚያደርጉ ተገልጧል። የቡሩንዲ ዋነኛ አደራዳሪ አሁንም የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ናቸው። ቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ ለሦስተኛ የሥልጣን ዘመን እወዳደራለሁ ማለታቸውን ተከትሎ በተከሰተው ቀውስ ውስጥ እስካሁን እንደተዘፈቀች ነው። በአባል ሃገራት መካከል የንግድ ልውውጥ እንዲጎለብት እና የግብር አሠራር ቀለል እንዲል ለማድረግ የሚንቀሳቀሰው የምሥራቅ አፍሪቃ ማኅበረሰብ መሠረቱን ያደረገው አሩሻ ታንዛኒያ ውስጥ ነው።

ፋሲል ግርማ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አርያም ተክሌ