የምህረት አዋጁ መገባደድ እና የኢትዮጵያዉያን ሁኔታ
ዓርብ፣ ሐምሌ 14 2009ማስታወቂያ
እስካሁንም ግን ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸዉ ሳዉዲ ዉስጥ እንደሚኖሩ የሚገመተዉ ከመቶ ሺህ የሚበልጡ ኢትዮጵያዉያን ተጠቃለዉ ወደ ሀገር እንልገቡ ነዉ የሚነገረዉ። የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ ሀገር የተመለሱት ቁጥር 60 ሺህ እንደሚደርስ ይገልጻል። የመጓጓዣ ሰነድ ማለትም ሊሴ ፓሴ የወሰዱት ከ120 ሺህ እንደሚበልጡ ነዉ የተሰማዉ። ከሰሞኑ ያን ያህል እንቅስቃሴ እንደሌለ የጠቆመን ጅዳ የሚገኘዉ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የአዉሮፕላን ትኬት ዋጋ መናር ብዙዎቹን ተስፋ እንዳስቆረጠ ገልጾልናል። ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ ነብዩን አነጋግሬዋለሁ።
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ