1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሜርክል የአፍጋኒስታን ቆይታ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 4 2004

አፍጋኒስታን የዘመተው የጀርመን ጦር በታቀደለት ጊዜ አፍጋኒስታንን ለቆ መውጣት አለመውጣቱ እያነጋገረ ነው ። አፍጋኒስታን የሚገኙ የጀርመን ወታደሮችን ትናንት ሳይታሰብ የጎበኙት የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ጦራቸው በርግጥ በተያዘለት ጊዜ

https://p.dw.com/p/14K89
ምስል dapd


አፍጋኒስታን የዘመተው የጀርመን ጦር በታቀደለት ጊዜ አፍጋኒስታንን ለቆ መውጣት አለመውጣቱ እያነጋገረ ነው ። አፍጋኒስታን የሚገኙ የጀርመን ወታደሮችን ትናንት ሳይታሰብ የጎበኙት የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ጦራቸው በርግጥ በተያዘለት ጊዜ ከአፍጋኒስታን መውጣት መቻሉ አጠራጣሪ መሆኑን ነው የጠቆሙት ።  ወታደራዊ ጠበብት ግን ከአሁን በኋላ አፍጋኒስታን መቆየቱ ትርጉም የለውም ባይ ናቸው ። ሂሩት መለሰ
የጀርመን መራሂተ መንግሥት የአንጌላ ሜርክል  የትናንቱ አሰቀድሞ ያልተነገረ የአፍጋኒስታን ጉዞአቸው ዓላማ በዚያ የሚገኙ የጀርመን ወታደሮችን መጎብኘት ነበር ። ጉብኝታቸው ግን  አንድ የአሜሪካን ወታደር  በአፍጋኒስታን ሰላማዊ ሰዎች  ላይ የፈጸመው ጅምላ ግድያ በእጅጉ ጥላ ያጠላበት ነበር ። ማዛሪ ሸሪፍ የሠፈሩትን የጀርመን ወታደሮች  የጎበኙት ሜርክል አሜሪካዊው ወታደር  ባለፈው እሁድ 9 ህፃናትና ሴቶችን ጨምሮ  16 ሰላማዊ ስዎችን በመግደሉ የተሰማቸውን ሃዘን ለአፍጋኒስታኑፕሪዝዳንት ሃሚድ ካርዛይ ገለጸዋል ።

Angela Merkel in Afghanistan
ምስል picture-alliance/dpa


« ዛሬ እዚህ ማዛሪ ሸሪፍ ሆኜ ከፕሬዝዳንት ካርዛይ ጋር  ተነጋግሬያለሁ ። ትናንት ሰለደረሰው ግድያ የተሰማኝን ሃዘን ገልጫለሁ ። ካርዛያ በአፍጋኒስታን መራሹ ጦር ስር የሚገኘውን የጀርመን ጦር በተለይም በመልሶ ግንባታው ሥራ እጅግ እንደሚያደንቁ ነግረውኛል ። ይህንንም መልዕክት ለጀርመን ወታደሮች እንድነግር ጠይቀውኛል ። »
ሜርክል በትናንቱ የአፍጋኒስታን ጉብኝታቸው ከፕሬዝዳንት ካርዛይ ጋር መዲናዋ ካቡል ውስጥ ፊት ለፊት ተገናኝተው አልተነጋገሩም ። ሁሉም ነገር ያለቀው የጀርመን ጦር   ከሚገኝበት ከሰሜን አፈጋኒስታኑ ከማዛሪ ሸሪፍ ዋና ጦር ሰፍር በስልክ ነበር ። በዚሁ ንግግራቸውም  ለፕሬዝዳንት ካርዛይ ያልተጣሩ ነገሮችን ግልፅ የሚያደርጉ መሆናቸውን  ከማረጋገጣቸውም በላይ አንደታቀደው እጎአ እስከ 2014 ዓም መጨረሻ ድረስ ባለው ጊዜ የጀርመን ወታደሮች ከአፍጋኒስታን ተጠናቅው ሲወጡ  በሁለቱ አገራት መካከል የወደፊቱ የጋራ ትብብር ስምምነት እንደሚፈረም ቃል ገብተውላቸዋል  ።

Afghanistan Deutschland Bundeskanzlerin Merkel zu Kurzbesuch in Masar-i-Sharif
ምስል dapd

ሜርክል እንዳሉት  ጀርመን ከአፍጋኒስታን ጋር ወደፊት በመልሶ ግንባታው ዘርፍ ይበልጥ ተትባበራለች   ።
« ጥርጣሬ መኖሩን ተገንዝቤያለሁ ። ምክንያቱም እያንዳንዱ የተናጠል እርምጃ ህዝቡን በተደጋጋሚ ግር ያሰኘዋል ። እና ሌላው ለአፍጋኒስታን ህዝብ ልናስገነዝበው የምንፈልገው ጠቃሚ ጉዳይ ፈጽሞ አንተዋችሁም ። በ 2014 ከሃገራችሁ ከወጣን በኋላ አፍጋኒስታንን መለሶ የመገንባቱን ተግባር እንገፋበታለን ። ለማሠልጠኑም ተግባር ሁል ጊዜ ዝግጁ ነን ።  እንደሚመስለኝ ይሄ በጣም ጠቃሚ መልዕክት ነው ። »

በሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት በምህፃሩ NATO መራሹ የአፍጋኒስታን ዘመቻ የጀርመን ወታደሮች ከተሰለፉ  10 ዓመት ተቆጠረ  ። ከዚህ ቀደም በተያዘው እቅድ የጀርመን ወታደሮች እጎአ በ 2013/ 2014  አፍጋኒስታን ለቀው ይወጣሉ ተበሎ እየተጠበቀ ነው ። ይሁንና ሜርክል ትናንት አፍጋኒስታን ውስጥ እንደተናገሩት የጀርመን ወታደሮች ከአፍጋኒስታን የሚወጡበትን ጊዜ ይህ ነው ብሎ መናገሩ አሰቸጋሪ ነው  ።

Afghanistan Deutschland Bundeskanzlerin Merkel zu Kurzbesuch in Masar-i-Sharif
ምስል dapd


« ሁኔታው በዛሬው እለት ነቅለን እንወጣለን ብሎ መናገር የማይቻልበት ነው ። ስለሆነም እስከ 2013 /2014 ይሳካልናል ብዮ መናገር አልቸልም ። በጎ ፈቃደኝነቱ አለ ። ያን ማከናውን እንሻለን ። »
ሜርክል ያን ቢሉም የጀርመን  ወታደሮች ከአፍጋኒስታን ይወጣሉ የተባለበት ጊዜ ግን አካራካሪ ሆኗል ። አንዳንድ ወታደራዊ ጠበብት የወታደሮቹ መዘገይት ትርጉም የለሽ ነው እያሉ ነው ። በነረሱ አባባል በአፍጋኒስታኑ ጦርነት ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎ ቢያንስ እስካሁን ምንም ውጤት አልተገኘም ። የአፍጋኒስታኑ ዓለም ዓቀፍ ዘመቻ ዓላማው አፍጋኒስታንን ማረጋጋት ቢሆንም  በአካባቢው

Afghanistan Deutschland Bundeskanzlerin Merkel zu Kurzbesuch in Masar-i-Sharif
ምስል dapd

የሚንቀሳቀሱት አክራሪ ኃይላት ጠንካራ ተፋላሚ ሆነው ቀጥለዋል  ። ሰለዚህም ይላሉ እነዚህ ወገኖች የጀርመን ጦርም ሆነ የሌሎቹ ሐገራት ባልደረቦች እስከ 2014 አፍጋኒስታን መቆይታቸው ሌላ ጥፋት መጋበዝ እንጂ የዘመቻው ዓላማ ግቡን ይመታል ተብሎ  አይታሰብም ። አፍጋኒስታን ከሚገኘው ዓለም ዓቀፍ ጦር  የጀርመን ወታደሮች በብዛት 3 ተኛውን ደረጃ ይይዛሉ ። በአሁኑ ጊዜም 4800 የጀርመን ወታደሮች በግዳጅ ላይ ናቸው

ሂሩት መለሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ