የሜርክልና የሜድዌዴቭ ውይይት8 ነሐሴ 2001ዓርብ፣ ነሐሴ 8 2001ሩስያው ፕሬዝዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ጋር ለመነጋገር ጥቁር ባህር ዳርቻ ወደ ምትገኘው ሶቺ ግዛት ያቀኑት የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ዛሬ በበርካታ ዓብይ ጉዳዮች ላይ ከፕሬዝዳንቱ ጋር ተወያይተዋል ።https://p.dw.com/p/JBY6ሜርክልና ሜድዌዴቭምስል APማስታወቂያመራሂተ መንግስትዋ በሩስያ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ እንደሚያሳስባቸው ከጉዞአቸው አስቀድመው ገልፀዋል ። ጀርመን ውስጥ የሚካሄደው የምርጫ ፉክክር እንዲሁም የምጣኔ ሀብት ችግር ከዚህ የሜርክል የሩስያ ጉብኝት ጀርባ እንዳለ ይገመታል ። ይልማ ኃይለ ሚካኤል ይልማ ኃይለ ሚካኤል/ ሂሩት መለሰ/ሸዋዬ ለገሠ